Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አቶ ማሞ ምህረቱ ከአሜሪካ የገንዘብ ሚኒስቴር  ምክትል ረዳት ጸሐፊ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ ከአሜሪካ የገንዘብ ሚኒስቴር  ምክትል ረዳት ጸሐፊ ኤሪክ ሜየር ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በቅርቡ የተደረገውን የማክሮ ኢኮኖሚ እንዲሁም ብሄራዊ ባንክ እያከናወናቸው የሚገኙትን የገንዘብ እና የፋይናንሺያል ሴክተር ማሻሻያዎችን በተመለከተ ምክክር አድርገዋል፡፡

በተጨማሪም በሁለቱ ሀገራት መካከል የቆየውን የሁለትዮሽ የንግድ እና የኢንቨስትመንት ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መምከራቸውን ከባንኩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version