የሀገር ውስጥ ዜና

የአዲስ አበባ ከተማ የ2016 በጀት ዓመት አፈጻጸም ግምገማ መድረክ እየተካሄደ ነው

By Amele Demsew

August 09, 2024

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2017 በጀት ዓመት እቅድና የ2016 በጀት ዓመት የመንግስትና የፓርቲ ሥራ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ እየተካሄደ ነው፡፡

የአስተዳደሩ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ በ2016 በጀት ዓመት ከተያዘው አጠቃላይ እቅድ በአማካይ ከ91 በመቶ በላይ ማሳካት መቻሉን አንስተዋል፡፡

ስኬቶቻችንን በማላቅና በማስፋፋት፣ የጥንካሬዎቻችንን ምንጭ በመለየት እንዲሁም ጉድለቶቻችንን በመሙላት እና በማረም ለኑሮ የተመቸች ውብ ከተማ ለመገንባት የጀመርነውን ሥራ አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉም ገልጸዋል፡፡