አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በተያዘው የመኸር እርሻ በሰብል ለመሸፈን ከታቀደው 164 ሺህ ሔክታር ከ143 ሺህ የሚልቀው መሸፈኑን የጋምቤላ ክልል እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ አስታወቀ፡፡
ከዚህም ውስጥ 54 ሺህ 480 ሔክታሩ በኩታ-ገጠም መታረሱን የገለጹት የቢሮው ኃላፊ ኡጁሉ ሉዋል÷ በዘንድሮው የመኸር ወቅት ካለፉት ዓመታት የተሻለ ምርት እንደሚገኝ አመላካች ሁኔታዎች አሉ ብለዋል፡፡
የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚረዱና በምርምር የተደገፉ ሰብሎች መዘራታቸውን እና አርሶ አደሩን የመደገፍ ሥራም እየተከናወነ ነው ማለታቸውን የቢሮው መረጃ አመላክቷል፡፡