ቢዝነስ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ሽልማት ተበረከተለት

By Mikias Ayele

August 08, 2024

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን “የፕሬዚዳንቱ የሕይወት ዘመን ሽልማት” ተበረከተለት፡፡

ሽልማቱ አየር መንገዱ በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ለሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች ለሰጠው የላቀ አገልግሎት የተበረከተ መሆኑን የአየር መንገዱ መረጃ ያመላክታል፡፡

በፕሬዚዳንት ባይደን የተፈረመው የሽልማት ሰርተፍኬት በአትላንታ ለሚገኙ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተወካዮች ተበርክቷል፡፡