የሀገር ውስጥ ዜና

ከሕገ-ወጥ ነጋዴዎች የተወረሰ 800 ሺህ ሊትር ዘይት ለሸማቾች ህብረት ሥራ ማህበራት ተከፋፈለ

By Meseret Awoke

August 08, 2024

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጉለሌ ክፍለ ከተማ ከሕገ-ወጥ ነጋዴዎች የወረሰውን 800 ሺህ ሊትር ዘይት ለ10 የሸማቾች ህብረት ሥራ ማህበራት በዛሬው ዕለት አከፋፍሏል።

በመዲናዋ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ ጥቂት ነጋዴዎች መሰረታዊ የፍጆቻ እቃዎች ላይ ሕገ-ወጥ ተግባር እየፈፀሙ እንደሆነ መገለጹን የከንቲባ ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል።

የክፍለ ከተማው ንግድ ቢሮ ሃላፊ አቶ አንዱዓለም ክብረት ፥ የምግብ ዘይቱ የተወረሰው ሕገ-ወጥ ነጋዴዎች ሰው ሰራሽ እጥረት ለመፍጠር ምርቱን በድብቅ አከማችተው በመገኘታቸው ነው ብለዋል፡፡