የሀገር ውስጥ ዜና

በኦሮሚያ ክልል 143 ቀበሌዎችና ከተሞች ዳግም የኤሌክትሪክ አገልግሎት አገኙ

By Feven Bishaw

August 06, 2024

 

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል አራቱም የወለጋ ዞኖች በፀጥታ ችግር በመሰረተ ልማት ላይ በደረሰ ጉዳት ከአገልግሎት ውጭ የነበሩ 143 ቀበሌዎችና ከተሞች ዳግም ኤክትሪክ አገልግሎት አገኙ፡፡

አካባቢዎቹ እስከ 6 ዓመታት ከኤሌክትሪክ አገልግሎት ውጭ እንደነበሩም ተገልጿል፡፡

የተጎዱና የወደሙ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶችን መልሶ በመጠገን አገልግሎቱን ወደ ነበረበት ለመመለስ የሚደረገው ዘመቻ መቀጠሉን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት መረጃ አመላክቷል፡፡

በጥገና ሥራውም በምስራቅ ወለጋ ዞን 53 አካባቢዎች፣ በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን 36 ቀበሌዎች፣ በምዕራብ ወለጋ ዞን 35 አካባቢዎች እንዲሁም በቄለም ወለጋ ዞን 19 ቀበሌዎች ለዓመታት ያጡትን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ዳግም ማግኘታቸው ተጠቁሟል፡፡