Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የኮሪያ ጦርነት ኢትዮጵያውያን አርበኞች መታሰቢያ ሃውልት በመዲናዋ ቆመ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኮሪያ ጦርነት ዘማች የነበሩ የ2 ሺህ 482 ኢትዮጵያውያን አርበኞችን ስም የያዘ መታሰቢያ ሃውልት በአዲስ አበባ ከተማ ተሰራ፡፡

ከፈረንጆቹ 1950 እስከ 1953 በኮሪያ ጦርነት የተሳተፉ ኢትዮጵያውያን አርበኞች ስም የተቀረጸበት የመታሰቢያ ሃውልት አገልግሎታቸውን ለማክበር በአዲስ አበባ መቆሙን የደቡብ ኮሪያ የቀድሞ ዘማቾች ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

የ2 ሺህ 482 ዘማች አርበኞችን ስም ዝርዝር የያዘ የሃውልቱ ምረቃ ሥነ-ስርዓት የደቡብ ኮሪያ የቀድሞ ዘማቾች ጉዳይ ሚኒስትር ካንግ ጁንግ-አይ በተገኙበት መካሄዱም ነው የተገለጸው።

ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) መለያ ሰንደቅ ዓላማ ወደ ደቡብ ኮሪያ ወታደር ወይም የህክምና ድጋፍ ከላኩ 22 ሀገራት መካከል አንዷ ናት፡፡

የኮሪያ ጦርነት ለሦስት ዓመታት ቆይቶ ሁለቱ ኮሪያዎች በስምምነት ጦርነቱን ሊያቆሙ መቻላቸው ይታወሳል፡፡

ባለፈው ዓመት ሐምሌ ወር ላይ የኢትዮጵያ እና የደቡብ ኮሪያ መንግስታት ከኢትዮጵያ አርበኞች ማህበር ጋር በመሆን በኮሪያ ጦርነት የተሳተፉ የ2 ሺህ 482 አርበኞችን ስም ዝርዝር ለማረጋገጥ መዝገቦችን ማሰባሰብ እና የማረጋገጥ ስራ መጀመራቸው ተገልጿል።

የኢትዮጵያ የቀድሞ ወታደሮች ማህበር በጦርነቱ ከ3 ሺህ 500 በላይ ወታደሮች መሳተፋቸውን በመግለጽ፥ ሚኒስቴሩ በመታሰቢያ ሃውልቱ ላይ ተጨማሪ ስሞችን ለማከል ተጨማሪ ጥናቶችን ለማድረግ ማቀዱን ዮንሃፕ የዜና አገልግሎት ነው የዘገበው።

Exit mobile version