የሀገር ውስጥ ዜና

የነሐሴ ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ በነበረበት እንደሚቀጥል ተገለጸ

By Meseret Awoke

August 06, 2024

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የነሐሴ ወር 2016 ዓ.ም የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ በሐምሌ ወር በነበረበት ዋጋ እንደሚቀጥል የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የነዳጅ ማደያዎችም በሐምሌ ወር በነበረበት ዋጋ እንዲሸጡ ትዕዛዛ መተላለፉን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) አስታውቀዋል፡፡

በየደረጃው የሚገኘው የንግድ መዋቅራችን በነዳጅ ስርጭትና ሽያጭ ዙሪያ ጥብቅ ቁጥጥር እና ክትትል እያደረገ ነው ሲሉም ገልጸዋል፡፡