ስፓርት

አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ለፓሪስ ኦሊምፒክ ሲያደርግ የነበረውን ዝግጅት ማጠናቀቁን ገለፀ

By Mikias Ayele

August 05, 2024

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በፓሪስ ኦሊምፒክ በማራቶን ኢትዮጵያን የሚወክለው አንጋፋው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ለውድድሩ ሲያደርግ የነበረውን ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታውቋል፡፡

አትሌት ቀነኒሳ በማህበራዊ ትስስር ገፁ እንዳስታወቀው÷ ለፓሪሱ ኦሊምፒክ ሲያደርግ የነበረውን ዝግጅት አጠናቋል።

በዝግጀቱ አብረውት ለነበሩት የቡድን አሰልጣኞች፣ ለቡድኑ አባላት፣ ለቤተሰቦቹ እና በመላው ዓለም ለሚገኙ አድናቂዎቹ ምስጋናውን አቅርቧል፡፡

እንደ ቡድን ጠንካራ ዝግጀት ማድረጋቸውን የገለፀው አትሌት ቀነኒሳ፤ ጠንካራ የቡድን ስሜት ለመፍጠር የሚያስችል የልምምድ ጊዜ ማሳለፍ መቻላቸውን ገልጿል።

በፓሪስ እየተካሄደ በሚገኘው 33ኛው ኦሊምፒክ በወንዶች ማራቶን ውድድር አትሌት ቀነኒሳ በቀለ፣ ታምራት ቶላ እና ዴሬሳ ገለታ ኢትዮጵያን ወክለው የሚወዳደሩ አትሌቶች መሆናቸው ይታወቃል።