አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት ጋር በመተባባር 83 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ አድርጓል፡፡
በሚቀጥሉት ቀናት ኢትዮጵያውያኑን የመመለሱ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መገለጹንም የኤምባሲው መረጃ ያመላክታል፡፡
በጅቡቲ በኩል የሚደረግ ሕገ-ወጥ ስደት እጅግ አደገኛ ከመሆኑም በላይ በየቀኑ የብዙዎችን ሕይወት እያሳጣ እንደሚገኝ ተጠቁሟል፡፡
ስለሆነም ከጸጥታ አካላት ጋር በቅንጅት በመስራት የዜጎችን ሕይወት መታደግ እንደሚገባ ኤምባሲው አስገንዝቧል፡፡