አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ20 በላይ አባላትን የያዘ የቻይና ቱሪስቶች ቡድን በዛሬው ዕለት አዲስ አበባ ገብቷል፡፡
“ተች ሮድ”በተሰኘ የቻይና ድርጅት እና በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስተባባሪነት ለመጡት ቱሪስቶች የቱሪዝም ሚኒስትር ዴዔታ ስለሺ ግርማ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡
ቱሪስቶቹ በመጀመሪያ ዙር የመጡ ሲሆን÷በቀጣይም በርካታ ቁጥር ያላቸው ቱሪስቶች ከቻይና እንደሚመጡ የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡
የቱሪዝም ሚኒስቴር ቻይናውያን ኢትዮጵያን ለጉብኝት ምርጫቸው እንዲያደርጓት በሀገሪቱ ካሉ ቱር ኦፕሬተሮች ጋር የተለያዩ ሥራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ተጠቁሟል፡፡
ቱሪስቶቹ በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ በገበታ ለሸገርና ገበታ ለሀገር የተሰሩ አዳዲስ የቱሪስት መዳረሻዎችን ጨምሮ የተለያዩ ቦታዎችን እንደሚጎበኙ ተገልጿል፡፡