አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ግንባታው በ2007 ዓ.ም ቢጀመርም በመሐል ለረጂም ጊዜ በመቋረጡ የመልካም አሥተዳደር ጥያቄ ሆኖ የቆየው የማሻ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ተመረቀ፡፡
ለግንባታው ከ57 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ መደረጉን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡
በዛሬው ዕለትም በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር) ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል፡፡
ከክልሉ ምሥረታ ወዲህ መንግሥት በሰጠው ልዩ ትኩረት ግንባታው ተጠናቅቆ ለምረቃ መብቃቱ ተገልጿል፡፡
በሌላ በኩል ርዕሰ መሥተዳድሩ ከ400 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ለሚገነባው የማሻ ከተማ የንጹህ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክት መሠረተ ድንጋይ አስቀምጠዋል፡፡