የሀገር ውስጥ ዜና

በጎፋ ዞን በመሬት መንሸራተት ለተጎዱ ወገኖች 10 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር ድጋፍ ተደረገ

By ዮሐንስ ደርበው

August 04, 2024

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ዋና ጽሕፈት ቤት በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎዱ ወገኖች የሚውል 10 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ።

የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ ስምኦን ሙላቱ (ዶ/ር) በጉዳቱ ማዘናቸውን ገልፀው በቀጣይም ተጨማሪ ድጋፍ ለማድረግ ቃል መግባታቸውን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

የጎፋ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ ዳግማዊ አየለ (ኢ/ር) ቤተክርስቲያኗ እያደረገች ላላው ድጋፍ አመስግነዋል፡፡

በተመሳሳይ የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊንየም የሕክምና ኮሌጅ በአደጋው ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ከ2 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ ያለው የሕክምና ቁሳቁስ እና ሰብዓዊ ድጋፎችን ድጋፍ አድርጓል፡፡