አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕዝቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ እና የሐረሪ ክልልን ለነዋሪዎች ምቹ ለማድረግ የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ርዕሰ መሥተዳድር ኦርዲን በድሪ ገለጹ፡፡
በ2017 በክልሉ በሚከናወኑ የልማት ሥራዎች ላይ ሕዝባዊ ውይይት ተካሂዷል።
አቶ ኦርዲን በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር ሐረር የዕድሜዋን ያህል አለማደጓን በመግለጽ በቁጭት በመነሳት ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግ ወደ ሥራ ተገብቷል፤ ሥራውም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡
በመድረኩ ላይ የመወያያ ጽሑፍ ያቀረቡት በብልጽግና ፓርቲ የክልሉ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ጌቱ ወዬሳ በኩላቸው÷ የኮሪደር ልማት ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል።
እየተከናወኑ ለሚገኙት እና ለነዋሪዎች ምቹ ከባቢን ለመፍጠር ዓልመው በቀጣይ ለሚሠሩ የልማት ሥራዎች ሕዝቡ የሚጠበቅበትን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ጠይቀዋል፡፡
የውይይቱ ተሳታፊዎችም የተጀመሩት ሥራዎች አበረታች ሆነው ማየታቸውን ገልፀው አሁንም ለልማቱ መረጋገጥ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንደሚያበረክቱ አረጋግጠዋል፡፡
በተሾመ ኃይሉ