አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ገቢዎች ሚኒስቴር እና ጉምሩክ ኮሚሽን ለክረምት የበጎ ፈቃድ ሥራ የሚውል 10 ነጥብ 1 ሚሊየን ብር ዋጋ ያለው የግንባታ ግብዓቶችና አልባሳት ድጋፍ አደረጉ፡፡
ድጋፉም ሲሚንቶ፣ ሚስማር፣ ፌሮ፣ የቤት ክዳን ቆርቆሮ እና አልባሳት ሲሆን÷ በለሚኩራ ክፍለ ከተማ በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ለሚከናወነው የአረጋውያንና አቅመ ደካሞች ቤት እድሳት የሚውል ነው ተብሏል፡፡