Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ግርማ አመንቴ(ዶ/ር) በአሶሳ ዞን የግብርና ልማትን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ(ዶ/ር)ን ጨምሮ ከፍተኛ የፌዴራልና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አመራር አባላት በአሶሳ ዞን የግብርና ልማት እንቅስቃሴን ጎብኝተዋል፡፡

ትናንት በተጀመረው የግብርና ሚኒስቴር፣ የክልል ግብርና ቢሮዎች እና ተጠሪ ተቋማት የጋራ ምክክር መድረክ ተሳታፊዎች በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ዞን በሚገኙ ወረዳዎች ጉብኝት አድርገዋል።

ጉብኝቱም በክልሉ የ2016/2017 የመኸር እርሻ የለማ በቆሎ ክላስተር፣ የአትክልት እና ፍራፍሬ ክላስተር እንዲሁም የሌማት ትሩፋት ስራ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ፈቃዱ ወየሳ ገልጸዋል።

የጉብኝቱ ተሳታፊዎች በጉብኝቱ ማብቂያ የችግኝ ተከላ ማካሄዳቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።

Exit mobile version