Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቱርኪዬ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቱርኪዬ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃካን ፊዳን ጋር ተወያዩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ዛሬ ጠዋት የቱርኪዬ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃካን ፊዳንን ተቀብዬ አነጋግሬያለሁ ብለዋል።

ውይይታችን ተጠናክረው በቀጠሉት የሁለቱ ሀገሮቻችን የሁለትዮሽ ግንኙነቶች ላይ ያተኮረ ነበር ሲሉም ገልጸዋል።

Exit mobile version