አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በፓሪስ ኦሊምፒክ በ800 ሜትር ሴቶች ማጣሪያ አትሌት ፅጌ ዱጉማና ወርቅነሽ መሰለ ወደ ግማሽ ፍፃሜ አልፈዋል፡፡
ምሽት 2 ሠዓት ከ45 ላይ 800 ሜትር የሴቶች ማጣሪያ ውድድር ተካሂዷል፡፡
በዚህም በምድብ ሁለት አትሌት ወርቅነሽ መሰለ 1፡58.07 እንዲሁም በምድብ ሶስት አትሌት ፅጌ ድጉማ 1፡57.90 በመግባት ግማሽ ፍጻሜውን ተቀላቅለዋል።
አትሌት ሀብታም ዓለሙ በሁለተኛ ዙር ማጣሪያ ወደ ግማሽ ፍጻሜ ለማለፍ ነገ በድጋሚ ትወዳደራለች።