አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በፓሪስ ኦሎምፒክ 5 ሺህ ሜትር ሴቶች ማጣሪያ አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ፣ እጅጋየሁ ታዬና መዲና ኢሳ ለፍፃሜ አልፈዋል፡፡
ምሽት 1 ሠዓት ከ10 ላይ በ5 ሺህ ሜትር ሴቶች ማጣሪያ ተካሂዷል፡፡
በዚህም በምድብ አንድ አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ 14፡57፡84፣ አትሌት እጅጋየሁ ታዬ 14፡57፡97 በሆነ ሰዓት በመግባት ለፍፃሜው ማለፋቸውን አረጋግጠዋል፡፡
እንዲሁም በምድብ ሁለት አትሌት መዲና ኢሳ 15፡00፡82 በሆነ ሰዓት በመግባት ለፍጻሜ አልፋለች።
በሌላ መርሐ-ግብር ደግሞ ምሽት 2 ሠዓት ከ45 ላይ በ800 ሜትር ሴቶች ማጣሪያ አትሌት ፅጌ ዱጉማ፣ ሀብታም ዓለሙ እና ወርቅነሽ መለሰ ኢትዮጵያን ወክለው ይወዳደራሉ።