Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በ1 ሺህ 500 የወንዶች ማጣሪያ ውድድር ኤርሚያስ ግርማና ሳሙኤል ተፈራ ወደ ግማሽ ፍጻሜ አለፉ

PARIS, FRANCE - AUGUST 02: Ermias Girma of Team Ethiopia celebrates winning the during the Men's 1500m Round 1 Heat 2 on day seven of the Olympic Games Paris 2024 at Stade de France on August 02, 2024 in Paris, France. (Photo by Christian Petersen/Getty Images)

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ33ኛው ኦሊምፒክ ጨዋታዎች የ1 ሺህ 500 ሜትር የወንዶች ማጣሪያ ውድድር ኤርሚያስ ግርማ እና ሳሙኤል ተፈራ ወደ ግማሽ ፍጻሜ አልፈዋል፡፡

በምድብ ሁለት የተወዳደረው ኤርሚያስ 3 ደቂቃ ከ35 ሴኮንድ ከ21 ማይክሮ ሴኮንድ በመግባት ነው ውድድሩን በቀዳሚነት በማጠናቀቅ ለግማሽ ፍፃሜ የበቃው፡፡

በተመሳሳይ በምድብ ሶስት በዚሁ ርቀት የተወዳደረው ሌላኛው አትሌት ሳሙኤል ተፈራ 3 ደቂቃ ከ37 ሴኮንድ ከ34 ማይክሮ ሴኮንድ በመግባት ስድስተኛ ደረጃን በመያዝ ወደ ግማሽ ፍጻሜው የገባው።

በምድብ አንድ የተወዳደረው አትሌት አብዲሳ ፈይሳ 14ኛ ደረጃን በመያዝ ማጣሪያውን ሳያልፍ ቀርቷል፡፡

Exit mobile version