የሀገር ውስጥ ዜና

ስርዓተ ትምህርቱ የሀገሪቱን ተጨባጭ ሁኔታ መሠረት ያደረገ ነው – ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)

By Tamrat Bishaw

August 02, 2024

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 26፣ 2016(ኤፍ ቢ ሲ) ስርዓተ ትምህርቱ የሀገሪቱን ተጨባጭ ሁኔታና ቀጣይ ጊዜያትን መሠረት ያደረገ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትር ብርሀኑ ነጋ (ፕ/ር) አስታወቁ።

የትምህርት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሰራተኞች በዓመታዊ ዕቅድ አፈጻጸም ዙሪያ ውይይት አድርገዋል፡፡

በመድረኩ የአጠቃላይ ትምህርት፣ የከፍተኛ ትምህርት፣ የኢትዮጵያ ትምህርት ባለስልጣንና የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዕቅድ አፈጻጸም ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

በውይይቱም ሥርዓተ ትምህርቱ የሀገሪቱን የአሁንና የመጪውን ጊዜ ፍላጎት እንዲሁም ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነትን ማዕከል የሚያደርግ መሆኑን ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

የአንድ ሀገር ስርዓተ ትምህርት የሀገርን የረጅም ጊዜ ጥቅም ማስጠበቅ የሚችሉ ዜጎች ማፍራት መሆኑንም ተናግረዋል።

ሰራተኛው ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ተፅዕኖ ነጻ ሆኖ በችሎታውና በብቃቱ ብቻ ህዝብና ሀገረ መንግስትን ማገልገል እንደሚጠበቅበት ማስገንዘባቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።