አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ33ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች ኢትዮጵያ የምትጠበቅበት የ10 ሺህ ሜትር የወንዶች ሩጫ ፍጻሜ ዛሬ ይካሄዳል፡፡
የ10 ሺህ ሜትር የወንዶች ሩጫ ፍጻሜ ከምሽቱ 4 ሠዓት ከ 20 ላይ እንደሚካሄድ የወጣው መርሐ-ግብር ያመላክታል፡፡
የማሸነፍ ቅድመ ግምት የተሰጣት ኢትዮጵያም በፍጻሜው በአትሌት ሰለሞን ባረጋ፣ ዮሚፍ ቀጄልቻ እና በሪሁ አረጋዊ ትወከላለች።