ስፓርት

ዩናይትድ የቅድመ ውድድር ዝግጅቶች ላይ ወሳኝ ተጫዋቾቹ ከሜዳ የሚያርቃቸውን ጉዳት አስተናገዱ

By Mikias Ayele

August 01, 2024

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በማንቼስተር ዩናይትድ አዲሱ ፈራሚ ሌኒ ዮሮ እና ራስመስ ሆይለንድ እና ሌሎች ተጫዋቾቹ ረዘም ላለ ጊዜ ከሜዳ እንደሚርቁ ተነግሯል።

ከፈረንሳይ ክለብ ሊል በ58 ነጥብ 9 ሚሊየን ዩሮ ማንቼስተር ዩናይትድን የተቀላቀለው ሌኒ ዮሮ ክለቡ ከአርሰናል ጋር በነበረው የወዳጅነት ጨዋታ ባጋጠመው ጉዳት ለሶስት ወራት ከሜዳ እንደሚርቅ ክለቡ አስታውቋል፡፡

በተመሳሳይ የፊት መስመር አጥቂው ራስመስ ሆይለንድ ባጋጠመው የቁርጭምጭሚት ጉዳት ለስድስት ሳምንታት ከሜዳ እንደሚርቅ ተረጋግጧል፡፡

በዚህም ሁለቱ ወሳኝ የቡድኑ ተጫዋቾች ሊጀመር 16 ቀናት ብቻ በቀሩት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ለተወሰኑ የውድድር ሳምንታት ለክለባቸው የማይጫወቱ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በተመሳሳይ ማርከስ ራሽፎርድ እና አንቶኒ ዶሳንቶስ ማንቼስተር ዩናይትድ ከሪያል ቤቲስ ጋር ባደረገው የወዳጅነት ጨዋታ ባጋጠማቸው ጉዳት ተቀይረው መውጣታቸውን ጎል ዶት ኮም ዘግቧል፡፡

በዚህም ቀያይ ሴጣኖቹ በቅድመ ውድድር ዝግጅት ላይ እያለ ወሳኝ ተጫዋቾቹን በጉዳት ምክንያት ለማጣት ተገዷል።

ማንቼስተር ዩናትድ በፕሪየርሊጉ ቅድመ ውድድር በሚቀጥለው እሁድ በወዳጅነት ጨዋታ ከሊቨርፑል ጋር የሚጫወት ሲሆን፤ ነሐሴ 10 ድግሞ የኮሙዩኒቲ ሺልድ የዋንጫ ጨዋታውን ከከተማ ተቀናቃኙ ማንቼስተር ሲቲ ጋር ያደርጋል፡፡