Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የኢትዮ-ቻይናን የንግድ አጋርነት ለማጠናከር እየተሠራ መሆኑ ተመላከተ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያና ቻይና መካከል ያለውን የንግድና ኢንቨስትመንት አጋርነት ለማጠናከር የሚሠሩ ተግባራት ተጨባጭ ውጤት እያመጡ መሆኑን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

የኢትዮ-ቻይና የወዳጅነት ትብብር ኮሚቴ ያዘጋጀው 2ኛው የኢትዮ-ቻይና ወዳጅነት ትብብር መድረክ በአዲስ አበባ ተካሂዷል።

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽንና በኢትዮ-ቻይና የወዳጅነት ትብብር ኮሚቴ መካከልም የኢትዮጵያን የኢንዱስትሪ ሴክተር ለማጠናከር ያለመ የመግባቢያ ስምምነት ተፈርሟል፡፡

ኢትዮጵያ ባለፋት አምስት ዓመታት በውጭ ባለሃብቶች ተመራጭነቷ እያደገ መምጣቱን የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ሃና አርአያሥላሴ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የቻይና ባለሃብቶች በኢትዮጵያ በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች የሚያደርጉት ተሳትፎ እየጨመረ መምጣቱን ገልጸው÷ የኢትዮ-ቻይና ወዳጅነትና ትብብር ኮሚቴም የሁለቱ ሀገራት የንግድና ኢንቨስትመንት ትስስር ይበልጥ እንዲሳለጥ እያገዘ ነው ብለዋል፡፡

የኮሚቴው ሊቀ-መንበር ቤቲ ሱ በበኩላቸው ዛሬ የተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት ለኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ሴክተር ዕድገት አዎንታዊ ሚና እንዳለው አስረድተዋል፡፡

Exit mobile version