የሀገር ውስጥ ዜና

የጣሊያን መንግስት ለኢትዮጵያ የ25 ሚሊየን ዩሮ የገንዘብ ድጋፍ አደረገ

By Tamrat Bishaw

July 31, 2024

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጣሊያን መንግስት በኢትዮጵያ የአካባቢ ልማትና አረንጓዴ ኢኮኖሚ መርሐ ግብርን ለማሳካት የ25 ሚሊየን ዩሮ የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል፡፡

የድጋፍ ስምምነቱን የተፈራረሙት በኢትዮጵያ የጣሊያን አምባሳደር አጉስቲኖ ፓሌስ እና የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ ናቸው፡፡

ስምምነቱ በኢትዮጵያ የማቲ ፕላን ማስፈጸሚያ ቁልፍ ከሆኑት ጉዳዮች መካከል አንዱ መሆኑን ከኢትዮጵያ የጣሊያን ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ድጋፉ ለስራ ዕድል ፈጠራ፣ ለኢኮኖሚ እድገት እና ሀገሪቱ ለያዘችው የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት የሚውል እንደሚሆንም ተመላክቷል፡፡

የጣሊያን ማቲ ዕቅድ በፈረንጆቹ 2022 በጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ ይፋ የሆነ ዕቅድ ሲሆን፤ ዓላማው ሀገሪቱ ከአፍሪካ አህጉርና ሀገራቱ ጋር ያላትን ግንኙነት ማጠናከር ነው።