ዓለምአቀፋዊ ዜና

የሃማስ ከፍተኛ መሪ ቴኅራን ውስጥ ተገደሉ

By Meseret Awoke

July 31, 2024

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሃማስ ከፍተኛ የፖለቲካ ኃላፊ ኢስማኢል ሃኒዬህ በኢራን መዲና ቴኅራን ውስጥ መገደላቸው ተሰምቷል፡፡

ሃኒዬህ እና አንድ ጠባቂያቸው የተገደሉት ከአዲሱ የኢራን ፕሬዚዳንት መስኡድ ፔዜሽኪያን በዓለ-ሢመት በኋላ ባረፉበት ቤት በተፈጸመ ጥቃት መሆኑ ተገልጿል።

የኢራን አብዮታዊ ዘብ እንዲሁም ሃማስ የሃኒዬ መሞታቸውን አረጋግጠዋል።

በዚህም ግድያውን አስመልክቶ ምርመራ እየተደረገ መሆኑን የተገለጸ ሲሆን፥ ተጨማሪ መረጃዎች ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡