አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የምክክር ተሳታፊዎች አጀንዳዎቻቸውን በይፋ ለኮሚሽኑ አስረክበዋል፡፡
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ላለፉት ሠባት ቀናት ሲካሄድ የነበረው የአጀንዳ ማሰባሰብና ለሀገራዊ ምክክሩ ጉባኤ ተወካዮች ምርጫ መድረክ ዛሬ ተጠናቋል፡፡
በዚህም ኮሚሽኑ የክልሉን አጀንዳዎች በተወካዮች አማካኝነት በይፋ የተረከበ ሲሆን ፥ በሂደቱ ተሳታፊ ከነበሩ የክልሉ ባለድርሻ አካላት 172 ተወካዮች ለሀገራዊ የምክክር ጉባኤ መመረጣቸውን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡