አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አቶ አሻድሊ ሀሰን በድጋሚ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው በምክር ቤቱ ተሹመዋል።
ምክር ቤቱ እያካሄደ ባለው 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት 1ኛ የሥራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤ አቶ አሻድሊ ሀሰንን በድጋሚ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ በሙሉ ድምጽ ሾሟል።
እንዲሁም አቶ ጌታሁን አብዲሳ በድጋሚ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የክልሉ ሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ኃላፊ ሆነው በምክር ቤቱ ተሹመዋል።
አቶ ጌታሁን አብዲሳም በምክር ቤቱ ፊት ቃለ መሐላ ፈጽመዋል።