አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የስፔኑ ባርሴሎና የእግር ኳስ ቡድን የስፖርት ባለሙያዎች ልዑክ በአዲስ አበባ ተገኝቶ መቻል የስፖርት ቡድንን ጎብኝቷል፡፡
በዚሁ ወቅትም ስለመቻል አመሠራረት ታሪክ፣ አሁናዊ አቋም እና በቀጣይ ዕቅድ ላይ ገለፃ ተደርጎለታል፡፡
የልዑኩ አባላትም በቀጣይ ከመቻል ጋር በተለያዩ የስፖርት ዓይነቶች በትብብር መሥራት እንደሚፈልጉ ማረጋገጣቸውን የመከላከያ ሠራዊት ማኅበራዊ ትስስር ገጽ መረጃ አመላክቷል፡፡
በተጨማሪም ከባርሴሎና አሰልጣኞችን በማምጣት ከመቻል ጋር የልምድ ልውውጥ እንዲደረግ እንሠራለን ብለዋል፡፡
ልዑኩ የመለያ እና ኳስ ድጋፍ ያደረገ ሲሆን በቀጣይም የስፖርት ትጥቆችንና ቁሶችን እንደሚለግስ አረጋግጧል፡፡