የሀገር ውስጥ ዜና

ሚኒስቴሩ ለጎፋ ዞን ከ6 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ አደረገ

By Tamrat Bishaw

July 29, 2024

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ(ኢ/ር) የተመራ ልዑክ በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በመሬት መንሸራተት ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች ከ6 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የአይነት ድጋፍ አደረገ።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ክልሉ በዘላቂነት ችግሩን ለመፍታት በሚሰራው ስራ የተለመደ ድጋፍና ትብብሩን እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

ድጋፉን ያስረከቡት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ (ኢ/ር)በአደጋው ለደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ሀዘን ገልፀው ለተጎዱ ወገኖች መፅናናትን መመኘታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።