ቢዝነስ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ከ7 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ አገኘ

By Melaku Gedif

July 29, 2024

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በ2016 በጀት ዓመት 7 ነጥብ 02 ቢሊየን ዶላር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ፡፡

የግሩፑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው በሰጡት መግለጫ÷ አየር መንገዱ የዓለም አቀፍ መዳረሻውን ወደ 139 ማሳደጉን ተናግረዋል፡፡

የሀገር ውስጥ በረራ መዳረሻውም 22 መድረሱን ነው የገለጹት፡፡

ፈጣን፣ ተመራጭ እና አስተማማኝነቱን እያረጋገጠ የመጣው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የእድገት ጉዞው ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉም አስገንዝበዋል፡፡

የያቤሎ፣ ሚዛን አማን፣ ጎሬ መቱ፣ ነጌሌ ቦረና እና ደብረ ማርቆስ የአውሮፕላን ማረፊያዎች በቀጣይ ዓመት አጋማሽ ጀምሮ አንደሚጠናቀቁ ተመላክቷል፡፡

በማርታ ጌታቸው