የሀገር ውስጥ ዜና

የዓለም ገንዘብ ድርጅት ለኢትዮጵያ የ2 ነጥብ 9 ቢሊየን ዶላር ድጋፍ አደረገ

By Tibebu Kebede

December 17, 2019

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 2፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም ገንዘብ ድርጅት ለኢትዮጵያ የ2 ነጥብ 9 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ ማድረጉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ አስታወቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በፌስ ቡክ ገጻቸው እንዳስታወቁት የዓለም ገንዘብ ድርጅት (አይ.ኤም.ኤፍ) ለኢትዮጵያ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም ማስፈጸሚያ የሚውል የ2 ነጥብ 9 ቢሊየን ዶላር ድጋፍ ለማድረግ ወስኗል።