አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) እስራኤል በጎላን ተራራ ሂዝቦላ አድርሶብኛል ያለችውን ጥቃት ተከትሎ ሊባኖስን በቦንብ መደብደቧ ተነግሯል፡፡
የእስራኤል ጦር በማእከላዊ ዴር ኤል ባላ ውስጥ ለመስክ ሆስፒታል እና ለመጠለያነት በሚያገለግል ትምህርት ቤት ላይ ጥቃት በመሰንዘር 15 ህጻናትን ጨምሮ 30 ሰዎችን ለህልፈት ዳርጓል ነው የተባለው።
ሂዝቦላህ በእስራኤል በተያዘው ጎላን ተራራ በሚገኘው ማጅዳል ሻምስ ከተማ ሮኬት በመተኮስ 12 የድሩዝ ማህበረሰብ ወጣቶችን መግደሉ ተመላክቷል፡፡
ጥቃቱን ተከትሎም የእስራኤል ጦር በደቡብ እና ምስራቅ ሊባኖስ የሚገኙ መንደሮችን እና ከተሞችን በቦምብ ደብድቧል።
እስራኤል ለተፈፀመባት ጥቃት ሂዝቦላን ተጠያቂ ታድርግ እንጂ የሊባኖስ ቡድን ለሮኬት ጥቃቱ ኃላፊነት አለመውሰዱን አልጀዚራ ዘግቧል።