አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀረሪ ክልል ምክር ቤት እያካሄደ በሚገኝው 6ኛ ዙር 3ኛ አመት 6ኛ መደበኛ ጉባኤ የቀረበለትን የካቢኔ አባላት ሹመት ተቀብሎ አጽድቋል።
የካቢኔ አባላት ሹመት በምክር ቤቱ የጸደቀው በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ አቅራቢነት ነው።
በዚህ መሰረትም
1ኛ.አቶ ሙክታር ሳሊህ- በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ
2ኛ.አቶ ጌቱ ነገዎ – የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ
3ኛ.አቶ ኢሊያስ ዮኒስ የሀረር የከተማ ማዘጋጃ ቤት ስራ አስኪያጅ
4ኛ.ወ/ሮ ዚነት ዩሱፍ- የክልሉ ሲቪል ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ
በተጨማሪም በክልሉ ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ አቶ አሪፍ መሀመድ አቅራቢነት
ወ/ሮ ደሊላ ዩሱፍ- የክልሉ ምክር ቤት የማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሆነው እንዲያገለግሉ ምክር ቤቱ በሙሉ ድምፅ አጽድቋል።
እንዲሁም ምክር ቤቱ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ አቅራቢነት ወይዘሮ አሻ አሚኔንን የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት በማድረግ ሹመት ሰጥቷል፡፡
ተሿሚዎቹም በምክር ቤቱ ቃለ መሀላ መፈፀማቸውን የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
የክልሉ ምክር ቤት ለሁለት ቀናት ሲያካሂድው የቆየው 6ዙር 3ኛ አመት 6ኛ መደበኛ ጉባኤ አጠናቋል።