Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የሶማሌ ክልል በድሬዳዋ በእሳት አደጋ ምክንያት የተጎዱ ወገኖችን ለማቋቋም 20 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል በድሬዳዋ አሸዋ ገበያ በቅርቡ በደረሰ የእሳት አደጋ ምክንያት ለጉዳት የተዳረጉ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም የ20 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል።

የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ በድሬዳዋ አሸዋ ገበያ የደረሰውን አደጋ በስፍራው ተገኝተው የተመለከቱ ሲሆን÷ ተጎጂዎችንም አፅናንተዋል።

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ተጎጂዎችን በጊዜያዊነት እና በዘላቂነት ለማቋቋም እያደረገ ያለውን ጥረትም አበረታተዋል።

ይህ እንቅስቃሴ ስኬታማ እንዲሆን በሶማሌ ክልል እና በነዋሪው ሥም 20 ሚሊየን ብር አበርክተዋል።

ድሬዳዋ የንግድና የኢንዱስትሪ ማዕከል ለመሆን የምታደርገው እንቅስቃሴ እንዲሳካም የክልሉ እገዛ ይጠናከራል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር÷ርእሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ እና የክልሉ ከፍተኛ አመራር አባላት በድሬዳዋ ተገኝተው ተጎጂዎችን በማፅናናታቸውና ተጎጂዎችን ለማቋቋም የሚደረገውን ጥረት በመደገፋቸው ምስጋና አቅርበዋል።

Exit mobile version