አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2016 ዓ.ም በጀት ዓመት 529 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 512 ነጥብ 82 ቢሊየን ብር መሰብሰቡን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ሚኒስቴሩ በ2016 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም እና በ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ ዙሪያ በአርባምንጭ ከተማ ውይይት እያካሄደ ነው፡፡
በዚህ ወቅት ሚኒስትሯ ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ÷ በ2016 በጀት ዓመት 529 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 512 ነጥብ 82 ቢሊየን ብር መሰብሰቡን ገልፀዋል።
በዚህም የእቅዱን 96 ነጥብ 88 በመቶ ገቢ መሰብሰቡን ያመላከቱት ሚኒስትሯ ከባለፈው ዓመት ገቢ ጋር ሲነፃፀርም በ70 ነጥብ 81 ቢሊየን ብር ብልጫ እንዳለው ተናግረዋል፡፡
የሀሰተኛ ደረሰኝ ህትመትና ስርጭት ቁጥጥር፣ የአገልግሎት አሰጣጥ ቅልጥፍና እና የቴክኖሎጂ ማሻሻያዎች ላይ የተደረጉ ለውጦች ለገቢው አስተዋፅኦ ያበረከቱ መሆናቸው ተመላክቷል፡፡
በቀጣይ በጀት ዓመትም ይበልጥ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ነው የተገለፀው፡፡
በዳዊት ጎሳዬ