ዓለምአቀፋዊ ዜና

የቻይና ፕሬዚዳንት በመሬት መንሸራተት ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖች የተሰማቸውን ሐዘን ገለጹ

By Mikias Ayele

July 27, 2024

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይና ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ሰሞኑን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ ሕይወታቸውን ላጡ ሰዎች የተሰማቸውን ሐዘን ገለጹ፡፡

ፕሬዚዳንት ሺ ለፕሬዚዳንት ሳኅለወርቅ ዘውዴ ባስተላለፉት የሐዘን መግለጫ÷  ለተጎጂ ቤተሰቦች መፅናናትን ተመኝተዋል፡፡