የሀገር ውስጥ ዜና

የአፋር ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ

By Meseret Awoke

July 27, 2024

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፋር ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር፣ 3ኛ የስራ ዘመን፣ 6ኛ መደበኛ ጉባኤውን በሠመራ ከተማ ማካሄድ ጀመረ።

በጉባኤው ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ፣ የክልሉን መንግስት የበጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም እያቀረቡ እንደሚገኙ የዘገበው ኢዜአ ነው።