አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔውን እያካሄደ ነው።
ምክር ቤቱ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በመሬት መንሸራተት አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ወጎኖች የኅሊና ጸሎት በማድረግ ነው ጉባኤውን የጀመረውን።
ምክር ቤቱ ከዛሬ ጀምሮ ለሁለት ቀናት በሚያካሂደው ጉባኤ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር የሚቀርበውን የክልሉ መንግስት የ2016 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም በማድመጥ ውይይት ያደርጋል ተብሏል።
በተጨማሪም የክልሉ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት፣ የጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ የዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርቶችን በማድመጥ ይወያያል።
በጉባኤው የክልሉን የ2017 በጀት ዓመት ማስፈጸሚያ በጀትን ጨምሮ በሚቀርቡ የተለያዩ ረቂቅ አዋጆች ላይ ተወያይቶ ያጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅም ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።