Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የሐረሪ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 3ኛ ዓመት 6ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል።

ምክር ቤቱ ለሁለት ቀናት በሚያካሄደው ጉባኤ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ እንደሚመክር ተጠቁሟል።

በጉባኤውም የክልሉ መንግስት የ2016 የስራ አፈጻጸም ሪፖርት እና 2017 በጀት ዓመት እቅድ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ እየቀረበ ሲሆን በምክር ቤቱ አባላት ውይይት ተደርጎበት ይጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

እንዲሁም የክልሉ የጠቅላይ ፍርድ ቤት እና የዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የ2016 ሪፖርት እና የ2017 በጀት ዓመት እቅድ ለጉባኤው ቀርቦም ውይይት እንደሚደረግበት ተመላክቷል።

የክልሉ መንግስት የ2017 በጀት ዓመት የሥራ ዘመን ማስፈጸሚያ በጀት ቀርቦ የሚጸድቅ ሲሆን፥ ምክር ቤቱ በሚያካሂደው ጉባኤ ላይ የተለያዩ ሹመቶችን እንደሚያጸድቅም ነው የተገለጸው።

ምክር ቤቱ ሰሞኑን በጎፋ ዞን በተከሰተው ድንገተኛ የመሬት መንሸራተት አደጋ ህይወታቸውን ላጡ ወገኖች የኅሊና ፀሎት አድርጓል።

በምንያህል መለሰ

Exit mobile version