አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግስት በጎንደር ከተማ እያከናወናቸው ስለሚገኙ የልማት ስራዎች የሚደግፍ፣ ለመንግስት እውቅና በመስጠት ምስጋና ለማቅረብ ህዝባዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።
የድጋፍ ሰልፉ በተለይ የፌደራል መንግስት ለከተማዋ ልማት ትኩረት በመስጠት ተቋርጠው የነበሩ ፕሮጀክቶች በማስቀጠል፣ አዳዲስ ፕሮጀክቶችን በመጀመሩ ለመንግስት እውቅና መስጠትና መደገፍን ዓላማው አድርጓል።
በህዝባዊ ሰልፉ የጎንደር እና አካባቢውን የረጅም ጊዜ የልማት ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት መንግስት ላሳየንን ቁርጠኝነት እውቅና እንሰጣለን፣ ለሰላማችን ዘብ እንቆማለን! የተጀማመሩ የልማት ስሳዎችን እናስቀጥላለን፣ የህዝብን ጥያቄ በማድመጥ ችግሮች በውይይት እና በድርድር ለመፍታት መንግስት ለሰላም ያሳየውን ቁርጠኝነት እንደግፋለን! የሚሉና ሌሎችም መፈክሮች ተስተጋብተዋል።
በህዝባዊ ሰልፉም የከተማዋ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች እየተሳተፉ ነው።
በጎንደር ከተማ የአፄ ፋሲል ቤተመንግስት እድሳትን ጨምሮ የኮሪደር ልማት ስራዎች፣ የመንገድ ግንባታና የውሀ ፕሮጀክቶችን ጨምሮ የተለያዩ የልማት ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ።
በሳሙኤል ወርቃየሁ