የሀገር ውስጥ ዜና

በትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዘርፍ የኢንቨስትመንት እድሎችና አማራጮች ላይ ውይይት ተካሄደ

By Shambel Mihret

July 26, 2024

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) ከዓለም አቀፉ የንግድና ፋይናንስ ተቋም ቡድን ጋር በትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዘርፍ የኢንቨስትመንት እድሎች እና አማራጮች ዙሪያ ተወያዩ፡፡

ሚኒስትሩ ከተለያዩ ሀገራት የተውጣጡ ባለሀብቶችን ያካተተው ቡድን ጋር የመከሩ ሲሆን÷ በውይይቱ በኢትዮጵያ የደረቅ ወደቦች መሠረተ ልማትና በሎጂስቲክስ ማዕከል ልማት ላይ መምከራቸው ተገልጿል፡፡

እንዲሁም ⁠በባቡር መሠረተ ልማት፣ በትራንስፖርት መሠረተ ልማትና አገልግሎት እንዲሁም ⁠በአቪዬሽን ዘርፍ ባሉ የኢንቨስትመንት ዕድሎች እና አማራጮች ዙሪያ ውይይት ማሄዱን አለሙ ስሜ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

ባለሀብቶቹ ኢትዮጵያ ባላት ዕምቅ ሀብት፣ ምቹ የቢዝነስ ከባቢ እና አዋጭ ገበያ በመሳብ በተለያዩ የዘርፉ ኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ለመሰማራት ፍላጎት እንዳላቸውም አረጋግጠዋል ተብሏል፡፡