Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አምባሳደሮች የኢትዮጵያን ክብር በማስጠበቅ ረገድ እንዲሠሩ የሚያስችል መመሪያ ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አምባሳደሮች በሚሠማሩበት መስክ እና ሀገራት የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅምና ክብር በማስጠበቅ ረገድ በትጋት በሚሠሩበት ሁኔታ ላይ ስምሪትና መመሪያ ተሰጠ፡፡

አዲስ ለተሾሙ አምባሳደሮች ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቅቋል፡፡

በማጠቃለያ መድረኩም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ተገኝተዋል፡፡

በመድረኩም አዲስ የተሾሙ አምባሳደሮች በሚሰማሩበት የሥራ መስክ የ100 ቀናት ዕቅዶቻቸውን አቅርበው ግምገማዊ ውይይት መደረጉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

አምባሳደሮቹ በሚሰማሩባቸው መስኮች እና ሀገራትም የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅምና ክብር በማስከበር ረገድ ሊያከናውኗቸው በሚገቡ ዋነኛ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የሥራና ስምሪት እና መመሪያ መሰጠቱ ተገልጿል፡፡

 

Exit mobile version