አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ገልጸዋል፡፡
አንቶኒዮ ጉተሬዝ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት የሃዘን መልዕክት÷ በጎፋ ዞን በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ ሕይወታቸውን ላጡ ዜጎች ጥልቅ ሃዘን አንደተሰማቸው ገልጸዋል፡፡