አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 12 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ንስር ማይክሮ ፋይናንስ ግማሽ ሚሊየን ብር የሚያወጡ የሙቀት መለኪያ መሳሪያዎችን ለጤና ሚኒስቴር ድጋፍ አደረገ፡፡
በርክክቡ ወቅት የጤና ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ እንደተናገሩት የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ለሚደረገው የተቀናጀ ርብርብ ድጋፍ በመደረጉ አመስግነዋል፡፡
ህብረተሰቡ የወረርሽኙን በፍጥነት መስፋፋት በመገንዘብ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
የንስር ማይክሮ ፋይናንስ ስራ አስኪያጅ አቶ ዳዊት ዋቅጋሪ በበኩላቸው የተበረከቱት መሳሪያዎች የሙቀት ልኬት መጠንን የሚያሳውቁ እና ከእጅ ንክኪ ነፃ የሆነ የእጅ ማፅጃ ሳኒታይዘር ያላቸው መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
ማሽኖቹ የሰዎችን ፎቶ በማንሳት እና አስፈላጊውን መረጃ በመያዝ የአንድሮይድ መልዕክት ማስተላለፍ የሚችሉ መሆናቸውን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡