ስፓርት

የካፍ የሴቶች ሻምፒየንስ ሊግ የሴካፋ ዞን የማጣሪያ ውድድር የምድብ ድልድል ይፋ ሆነ

By ዮሐንስ ደርበው

July 24, 2024

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የካፍ የሴቶች ሻምፒየንስ ሊግ የ2023 የሴካፋ ዞን የማጣሪያ ውድድር የምድብ ድልድል ይፋ መሆኑን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን አስታወቀ፡፡

በዚሁ መሠረት÷ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከኬንያ ፖሊስ ቡሌትስ፣ ዬ ጆይንት፣ ዋሪየርስ ኩዊንስ እና ራየን ስፖርት ውሜንስ ጋር በምድብ አንድ ተደልድሏል፡፡

እንዲሁም ሲምባ ኩዊንስ፣  ፒቪፒ  ቡየንዚ፣ ካወምፔ ሙስሊም ሌዲስ እና ፋድ ጅቡቲ በምድብ ሁለት መደልደላቸውን የፌደሬሽኑ መረጃ አመላክቷል፡፡

መርሐ-ግብሩ በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት እንደሚካሄድም ነው የተገለጸው፡፡