ዓለምአቀፋዊ ዜና

የ18 ሰዎችን ሕይወት ከቀጠፈው የአውሮፕላን አደጋ አብራሪው በሕይወት ተገኘ

By Meseret Awoke

July 24, 2024

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኔፓል ዋና ከተማ ካትማንዱ በተከሰተ የአውሮፕላን አደጋ አብራሪው በሕይወት ሲገኝ የ18 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተሰምቷል፡፡

በርካቶችን ከቀጠፈው ከዚህ አደጋ በሕይወት የተገኘው የአውሮፕላኑ አብራሪም በአሁኑ ወቅት የሕክምና ክትትል እየተደረገለት መሆኑ ተነግሯል፡፡

የአየር መንገዱን የቴክኒክ ሠራተኞች ጨምሮ 19 ሰዎች በሳውሪያ አየር መንገድ አውሮፕላን ተሳፍረው የቱሪዝም መዳረሻ ወደ ሆነችው ፖክሃራ ለማቅናት በረራ መጀመራቸው ተጠቅሷል፡፡

በዚህም ከመሬት በተነሳበት ቅጽበት “ወደ ቀኝ በመታጠፍ ላይ እንዳለ ከአውሮፕላን ማረፊያው በስተምሥራቅ በኩል ተከስክሶ በእሳት መያያዙን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡