የሀገር ውስጥ ዜና

ምክር ቤቱ በጎፋ ዞን በመሬት መንሸራተት አደጋ በደረሰው ጉዳት የተሰማውን ሀዘን ገለጸ

By Meseret Awoke

July 23, 2024

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ የተከሰተውን ድንገተኛ የመሬት መንሸራተት አደጋ ተከትሎ በደረሰው የሰው ህይወት መጥፋት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጿል፡፡

ምክር ቤቱ በአደጋው ጉዳት ለደረሰባቸው የተጎጂ ቤተሰቦች እና ዘመድ ወዳጆች ሁሉ መፅናናትን ተመኝቷል።