Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የተለያዩ ክልሎች በጎፋ ዞን በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ ሐዘናቸውን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ ክልሎች በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ የተከሰተው የመሬት መንሸራተት በሰዎች ላይ ባደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ሐዘን ገለጹ፡፡

በዚሁ መሠረት÷ የኦሮሚያ፣ ሲዳማ፣ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች ባወጡት የሐዘን መግለጫ÷ ትናንት በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ ምክንያት የሰው ሕይወት በማለፉ እና ሌሎች ወገኖችም በመፈናቀላቸው የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን ገልጸዋል፡፡

ለሟች ቤተሰቦች እና ወዳጅ ዘመዶች መጽናናትን የተመኙት ክልሎቹ÷ የተጎጂ ቤተሰቦችን ለማቋቋም በሚደረገው ጥረት ከክልሉ ሕዝብና መንግሥት ጎን እንደሚቆሙ አረጋግጠዋል፡፡

Exit mobile version