የሀገር ውስጥ ዜና

በኢትዮጵያና በተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች መንግስታት ለከፍተኛ አመራሮች የሚሰጥ ስልጠና መርሐ ግብር ትውውቅ ተካሄደ

By Meseret Awoke

July 23, 2024

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያና በተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች መንግስታት ለመንግስት ከፍተኛ አመራሮች የሚሰጥ ስልጠና መርሐ ግብር ትውውቅ ተካሂዷል፡፡

የመርሐ ግብሩ ትውውቅ የተካሄደው ከ”አምስት ሚሊየን ኢትዮጵያዊያን ኮደርስ” የማስጀመሪያ መርሐ ግብር ጎን ለጎን ነው ተብሏል፡፡

በዚህም ከተለያዩ የኢትዮጵያ መንግሥት ተቋማት ለተወጣጡ ከፍተኛ አመራሮች ለሥድስት ወራት የኤክስኪዩቲቭ ሊደርሺፕ ሥልጠና ለመስጠት የታለመበት መርሐ-ግብር ተዋውቋል።

ሥልጠናው በኢትዮጵያ እና በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች መንግሥታት በትብብር የሚሰጥ መሆኑን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።